100 ፕርሰንት ከካሎሪ ነፃ የሆነውን ውሃ በመጠቀም የሰውነት ክብደት እንዴት መቀነስ እንደምንችል የሚያሳይ ቪዲዮ

ውሃ የምግብ አፈጫጨት ስርዓትን ለማስተካከል ፣ የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ማገዝ ፣ ጭንቀትን ለመቀነስ ፣ አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጥ እና አዲስ የደም እና የጡንቻ ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋል፡፡

ከእነዚህም በተጨማሪ ውሃ በደም ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ነገሮችን ጠራርጎ በማስወጣት ቆዳችን ንጹህ፣ ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል ፣ የሊምፍ ሥርዓታችን (Lymph System) የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህም ማለት እነዚህ ዕጢዎች የዕለት ከዕለት ተግባራችንን በትክክል እንድንወጣ የሰውነታችን ፈሳሽ የተመጣጠነ እንዲሆን እና ኢንፌክሽንን እንድንዋጋ ይረዱናል፡፡

በተቃራኒው ሰውነታችን በቂ ውሃ ሳያገኝ ሲቀር የራስ ምታት ፣ ጥሩ ስሜት አለመሰማት ፣ ሀሳብን ለመሰብሰብ መቸገር ፣ ተደጋጋሚ የረሀብ ስሜት እንዲሁም ሰውነታችን ካርቦሀይድሬትን ወደ ሀይል በመቀየር ፋንታ ወደ አላስፈላጊ ስብ መቀየር ይሆናል ምርጫው፡፡ ስለዚህ ለመላው ጤናችን በየቀኑ በቂ ውሃ መውሰድ ይኖርብናል፡፡

ETHIOPIA – ውሃ ክብደትን ለመቀነስ | water for weight loss in Amharic